በመኮንን ተሾመ ቶሌራ
ኢትዮጵያ ውስጥ አፈር ሁሉንም ነገር ማለት ነው፡፡ ኢትዮጵያኖች አፈርን በተመለከተ ሀገር በቀል እውቀት አላቸው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ገበሬዎች ከከብቶችና ከአፈር ጋር ጥብቅ ቁርኝት ነው ያላቸው፡፡ ከብቶቻቸውን እንደ ሰው ያወሯቸዋል፡፡ በተለይም ደግሞ ለሚያርሱ በሬዎቻቸው መጠሪያ ስም ይሰጧቸዋል፡፡ የእርሻ መሬታቸው ላይ ካለው አፈር ጋር ያወጋሉ- ‹የህይወት መጀመሪያ› ሲሉም ይገልጹታል፡፡ ሁሉም ሰው ሲሞት አፈር እንደሚሆን ስለሚያውቁ ‹የእያንዳንዱ ሰው የመጨረሻ ቤት› ይሉታል፡፡ አፈር የህይወት መገኛ ነው፡፡ እናም ደግሞ የህይወት ዞሮ ማብቂያም ነው፡፡ አፈር ሁሉንም ነገር ነው፡፡
በምዕራብ ኢትዮጵያ በሚገኘው ጃማ ወንዝ ክልል ውስጥ ደግሞ አፈር ከፍተኛ አደጋ ተጋርጦበታል፡፡
መኮንን ተሾመ እባላለሁ፡፡ ልምድ እንዳለው የሳይንስ ጋዜጠኛ ሁሌም በታላላቅ የልማት ጉዳዮች ላይ አሰላስላለሁ፣ ጥናት አደርጋለሁ፤ እጽፋለሁ፡፡ ነገር ግን በ2021 ከኢንፎናይል ያገኘሁት የፎቶ ጋዜጠኝነት የስልጠና እድል ስለ ፎቶ ጋዜጠኝነት በንድፈ ሐሳብ የማውቀውን ግንዛቤ በተግባር ለመግለጽ አግዞኛል፡፡
ትልቁ የአባይ ወንዝ ገባር በሆነው በጃማ ወንዝ ዙሪያ ያለውን ከፍተኛ የአፈር መራቆት፣ የአፈር መሸርሸር እና የደን መራቆትን በተመለከተ እንድመራመር መንገድ ጠርጎልኛል፡፡
ከአዲስ አበባ በስተ ሰሜን ወደ 200 ኪሎ ሜት ርቀት ላይ ወደ ሚገኘው ወደ ጃማ ወንዝ በመጓዝም በአካባቢው ያለውን የአፈር መሸርሸር፣ የመሬት መራቆት፣ የደን መመናመን፣ የከሰል ንግድ እንዲሁም የአካባቢ ጥበቃና የእርከን ስራዎችን በምስል ማስቀረት ችያለሁ፡፡
በእውነት ለመናገር በጃማ ወንዝ ዙሪያ የተዘነጉ ደረቅ ቀጠናዎችን በአካል ተገኝቶ ማየትና መመስከር በጣም ስሜት የሚነካና የሚያስደንቅ ነው፡፡ አካባቢው በከፍተኛ ሁኔታ እየተራቆተ መሆኑና የአፈሩ ለም ያለመሆን ነገር የአካባቢው ነዋሪዎችን አስጨንቋቸዋል፡፡ እንዲያም ሆኖ የመልሶ ማልማት ስራቸው እና የችግኝ ተከላ ጥረታቸው ተፈጥሯዊው ለም አፈራቸውን መልሶ እንደሚያመጣላቸው ተስፋ ያደርጋሉ፡፡
የጃማ ወንዝ ወደ ብሉ ናይል የሚፈስ ትልቁ ገባር ወንዝ ነው፡፡
ብሉ ናይል እስከ ግብጽ ድረስ የሚፈሰው የአባይ ወንዝ ገባር ከሆኑት ሁለት ታላላቅ ወንዞች መካከል አንደኛው ነው፡፡ በኢትዮጵያና ሱዳን በኩል የሚጓዝ ሲሆን፤ በዝናብ ወቅት ለአባይ ወንዝ ወደ 85 በመቶ ያህል የሚያቀርብ ነው፡፡
ብሉ ናይል ወይም የአባይ ወንዝ የኢትዮጵያ ‹ሰማያዊው ወርቅ› ተብሎ ይታወቃል፡፡ ለምን ቢባል ከማዕከላዊ አፍሪካ ታላላቅ ሐይቆች ተነስቶ ከሚፈሰው ከነጩ ናይል ጋር ሲነጻጸር ብሉ ናይል ቀለሙም ሰማያዊ ነው፡፡ ብሉ ናይል (ሰማያዊው ወንዝ) መልኩ ሰማያዊ የሆነው ከኢትዮጵያ ለም መሬቶች ጠራርጎ በሚወስደውና በሚይዘው አፈርና ከባድ ደለል ምክንያት ነው፡፡ በሰማያዊው ወንዝ ተጠርጎ የሚወሰደው ሰማያዊ አፈራችንም ኑሯቸውን በአፈርና ውሀ ላይ በመሰረቱ ገበሬዎች ዘንድ እንደ ‹ወርቅ› ይቆጠራል፡፡ ‹‹ሰማያዊው ወርቅ›› የሚለው መጠሪያ መነሻው ይህ ነው፡፡
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ትልቅ የሆነውን የሀይል ማመንጫ የሆነውን ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን እየገነባች ነው፡፡ አሁን 80 በመቶ ያህል የተጠናቀቀው የዚህ ግድብ ዋንኛ ጠቀሜታ የኢትዮጵያን የኤሌትሪክ ሀይል እጥረት ለመቅረፍና ለጎረቤት ሀገሮች ሀይል ለመላክ ነው፡፡
በሀገር ውስጥ ገንዘብ የሚሰራው ፕሮጀክቱ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ቦታዎች ወደ አዲሱ ውሀ ማጠራቀሚያ በሚገቡ የአፈር ቅሪተ አካሎች የአደጋ ስጋት አጋጥሞታል፡፡ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የአፈር ቅሪተ አካል ፍሰቱ ለ100 አመት የሚይዝ ተደርጎ 100 years of sediment inflow, የተሰራ ሲሆን፤ የላይኛው ተፋሰስ መሬት መራቆት ግድቡን ሊያጨናንቅ የሚችል ከፍተኛ የአፈር ቅሪተ አካል ሊከሰት ይችላል፡፡
የአፈር ቅሪተ አካሎች ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ የሚንቀሳቀሱ ጠጣር ቁሶች ሲሆኑ፤ በወንዝ ፍሰት አማካኝነት ሊንቀሳቀሱ ይችላሉ፡፡ በውስጣቸውም ድንጋዮችን፣ ማዕድኖችን እና የእጽዋትና እንስሳት ተረፈ ምርቶችን ሊይዙ ይችላሉ፡፡ የእነሱ መንቀሳቀስ ተፈጥሯ ሂደት ሲሆን፤ ለታችኛው ተፋሰስ የማህበረሰብ ክፍሎች ለም አፈርን ያቀርባል፡፡
ነገር ግን መሬት ከመጠን በላይ በማረስ፣ በመጋጡ እና በደን መራቆት ሲሸረሸር ብዙ የአፈር ቅሪተ አካሎች ወደ ታችኛው ተፋሰስ ግድብ በሚፈስ ወንዝ ላይ ሊቀሩ ይችላሉ፡፡ የግድቡን ፍሰት የመቀነስ፣ የግድቡን መሰረተ ልማት የመጉዳት እና የግድቡን የማጠራቀሚያ እና የሀይል ምርትን የመቀነስ አቅም አላቸው፡፡
በጃማ ወንዝ ተፋሰሶች የውሀ ፍሰት ወደታች ወደ ሸለቆው በመጥለቅ እና ወደ ላይም ወደ ተራራማው ክፍል ድረስ መጓዙን እንደቀጠለ ነው፡፡
ኢትዮጵያ ከፍተኛ የደን መራቆት የሚታይባት ተራራማ ሀገር እንደመሆኗ መጠን፤ የአፈር መሸርሸር እና ደለል ለታችኞቹ ተፋሰስ ሀገሮች ለሱዳንና ግብጽ ትልቅ ችግር እየሆነባቸው ነው፡፡ የግብጽን አስዋን ግድብ እና የሱዳንን ሜሮይን ግድብን ጨምሮ በሀገራቱ የሀይል ማመንጫ እና የመስኖ ግድቦችቻቸው ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድር ነው፡፡
በ2014 ላይ ተመራማሪዎች ይፋ ያደረጉትና ‹‹በአባይ ተፋሰስ የአፈር መሸርሸር እና መካተት፤ ልምዶችና ፈተናዎች›› የተሰኘው ጥናት (study) የአፈር ቅሪተ አካሎች በኢትዮጵያ ድንበር በኩል ወደ ታችኛው ተፋሰስ ሀገሮች እንደሚሔዱ አረጋግጧል፡፡ ከሱዳን ጋር ባለው ድንበር የአፈር ቅሪተ አካሉ ክምችት በአንድ ሊትር 12.3 ግራም መሆኑ ተመዝግቧል፡፡
በመሬቱ መራቆት እጅጉን ባዝንም ይህንን አስደናቂ ተራራማ እና በረሀማ መልክዐምድር መመልከቴ እንደ ፎቶግራፍ ባለሞያና ጋዜጠኛ እጅግ አስደምሞኛል፡፡
ለስራ በምጓዝ ጊዜ ሁሉ እንደማደርገው በጃማ ወንዝ ዙሪያ የራሴንም የተራቆተውን የጃማ ወንዝ ዙሪያ ምስል በፎቶ አስቀርቻለሁ፡፡ ወዳጄ ጥበበስላሴ በዚህ የስራ ጉዞዬ ፎቶግራፎችን በማንሳት አግዞኛል፡፡ ሰው በቀላሉ ሊደርስበት የማይችለውና መጥፎ የሆነ የአየር ንብረት ያለውን አካባቢን መጎብኘት ፈጽሞ የማይረሳ ትዝታ ነው፡፡
ፎቶ ባለሞያው በጃማ ወንዝ ዙሪያ ያለውን የአፈር መሸርሸር እና መራቆት መጠን ለመረዳት ሰአታትን አሳልፏል፡፡
ለከሰልነት የሚቃጠሉ ዛፎች
በጃማ ወንዝ አካባቢ ከሰል ለንግድ እና ለምግብ ማብሰያነት ላሉ የቤት ውስጥ አገልግሎቶች ይመረታል፡፡ ምርቱ የሚጀምረው ዛፎችን በመቁረጥ ነው፡፡ ዛፎቹ ከተቆራረጡ በኋላም ለከሰልነት እንዲነዱ ይደረጋል፡፡ ይህም ለደን መመናመን እና በመጨረሻም ለአፈር መሸርሸር የበኩሉን አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡
በኢትዮጵያ ወደ 90 በመቶ የሚሆን የቤት ውስጥ የሀይል ምንጭ በተለይም ለምግብ ማብሰየነት የሚገኘው ሀይል በባህላዊ ባዮማስ እንደ ከሰል፣ ማገዶ እና አህል ካሉ የባዮማስ ውጤቶች ነው፡፡ ከ2000 እስከ 2013 ባለው ጊዜ በሀገሪቱ የከሰል ፍላጎት ከ48,581 ወደ 4,132,873 ቶን በአመት ያደገ ሲሆን፤ ይህም ከ85 በመቶ በላይ መጨመሩን ያመለክታል፡፡ ይህ የመሬት መራቂትና ደን መጥፋት መጠን በእጅጉን ማሻቀቡን አመላካች ነው ሲል የኢትዮጵያ አካባቢ እና ደን ጥናት ማዕከል ያካሔደው ጥናት (2020 study) ያመለክታል፡፡
በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ አካባቢ በመርሀ ቤቴ ወረዳ ሙላቱ ታዬ የተባለ የከሰል ነጋዴን አግኝቼ አናግሬው ነበር፡፡ ቀደም ሲል ገበሬ እንደነበረ አጫውቶኛል፡፡
‹‹ቀደም ሲል በአያቶቻችን ጊዜ አፈራችን በጣም ለም እና ፍሬ የሚሰጥ ነበር›› ሲል የሚያስታውሰው ታዬ፤ ‹‹አሁን ግን ተጠራርጎ እየተወሰደ እና ምርታማ አይደለም፡፡ አሁን የተወሰነ ሰብል ነው የምናመርተው፡፡ አባቴ ግን አፈሩ ለም በነበረ ጊዜ ሁሉንም አይነት ሰብል ያመርት ነበር፡፡ ግብርና ብቻውን ለአባቴ መተዳደሪያ በቂ ነበር፡፡ ለእኔ ግን ግብርና ብቻ በቂ መተዳደሪያ አልሆነም፡፡ ለዚህ ነው የከሰል ነጋዴ የሆንኩት›› ይላል፡፡
እነዚህ ጉማጅ ዛፎች አፈር መያዝ ከሚችለው ከስራቸው ጀምሮ የመቁረጥ ባህል እንዳለ ያመለክታሉ፡፡ የእነዚህ ዛፍ መመናመን በጃማ ወንዝ አካባቢ ሰፊ የሆነ የአፈር መሸርሸር እንዲከሰት አድርጓል፡፡
ኢካሊፕተስ የሚባሉት የዛፍ አይነቶች የሚቆረጡት ለቤት መስሪያነት ነው፡፡ በጃማ እና ጃራ ወንዝ ሸለቆ አካባቢ 14 አይነት ሀገር በቀል ዛፎች ይገኛሉ፡፡ (14 different types of tree, plant and shrub species) ሀገር በቀል ያልሆኑት የዛፍ አይነቶች ደግሞ ለማገዶነት የሚተከሉ ናቸው፡፡
የፎቶግራፍ ባለሞያው መኮንን ተሾመ በከፍተኛ በከፍኛ የአፈር ቅሪተ አካሎችና በአፈር መሸርሸር በተጎዳው በጃማ ወንዝ አካባቢ
አፈር ወደታች እንዳይወርድ በአካባቢ ማህረሰብ እርከን ተሰርቷል፡፡ ይህ ባይሆን ኖሮ ግን አካባቢው በአፈር መሸርሸር የተጋለጠ ይሆናል፡፡
አፈር እና ውሀ ለግብርና ለእንስሳት እና ሌሎች የልማት ጥረቶች አስፈላጊ የመሆኑን ያህል መሬት መሸርሸርን መቀነስ ደግሞ ፈታኝ ስጋት እንደሆነ አለ፡፡
የአፈር መሸርሸርን ለመቀነስ በአሁኑ ወቅት ብዙ አፈርና ውሀ ጥበቃ ተግባሮች በገበሬዎች እየተከናወኑ ነው፡፡ የኢትዮጵያ መንግስትም በአራት አመት ውስጥ 22 ቢሊዮን ዛፎችን ለመትከል እቅድ ይዞ በየአመቱ የዛፍ ተከላ ዘመቻዎችን እያደረገ ነው፡፡ በዚህ ዝናባማ ወቅትም በኢትዮጵያ ሰባት ሚሊዮን ዛፎችን seven billion trees ለመትከልም ታቅዷል፡፡
በጃማ ወንዝ ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች የእርሻ መሬታቸው ከመሸርሸር ለመጠበቅ እንዲህ አይነት እርከኖችን ሰርተዋል፡፡ ይህ ደግሞ አፈርና ውሀን ለመያዝና ምግብ ለማልማት የሚያስችል የአካባቢው ገበሬዎች የምህንድስና እና ማህበራዊ ተቋም ስኬታቸው ነው፡፡
በጃማ ወንዝ የደን መራቆት በከፍተኛ ቦታዎች የአፈር መሸርሸር በፍጥነት እንዲከሰት አድርጓል፡፡ የአካባቢው ማህበረሰብም በወንዙ አካባቢ ተክል ለመትከል እየሞከሩ ነው፡፡ በእርግጥ ጥረታቸው እስከአሁን ፍሬዎችን ባያፈራም፡፡
እንዲህ ያለው የዛፍ መትከል ጥረቶች ወደ መሬት የሚሰርገውን የዝናብ ውሀ በመቀነስ የአፈር መሸርሸርን ይከላከላል፡፡ የዝናብ ውሀው የዛፎቹን ቅጠሎችና ቅርንጫፎች ላይ በሚያርፍበት ጊዜ ወደ አፈሩ በዝግታ የሚገባ በመሆኑ በዝናብ የሚወሰደው የአፈር መጠን ይቀንሳል፡፡ እነዚህ ዛፎች በየጊዜው ዝናባማ ወቅት በአካባቢው አስተዳደሮች አማካኝነት የተተከሉ ናቸው፡፡
ቁጥቋጦዎች አፈር ከመሸርሸር እንዲድን ይተከላሉ፡፡ በጃማ ወንዝ ሸለቆ አካባቢ ያሉ አንዳንድ ቁጥቋጦዎች ሀገር በቀል (shrub plants native) ሲሆኑ፤ የወንዝ ዳር ቁጥቋጦዎችና ባለአበባ ቁጥቋጦዎች የተሰኙ ተክሎች ይገኙበታል፡፡
የፎቶግራፍ ባለሞያው መኮንን ተሾመ በዚህ በኦሮሚያ እና አማራ ክልል መካከል በሚገኘው ደረቅ አካባቢ ሶስት ቀናት ካሳለፈ በኋላ ወደ አዲስ አበባ ለመመለስ የ200 ኪሎ ሜትር ጉዞውን ጀምሯል፡፡ በመንገዱ አስቸጋሪነት የተነሳም በመኪና ወደ 7 ሰአት አካባቢ ይፈጅበታል፡፡
ወደ ጃማ ወንዝ ያደረኩት ጉዞ ጥሩ ልምድ ያገኘሁበት ነበር፡፡ ጉዞዬን ያጠናቀቅኩትም በከፍተኛ ተስፋ ነው፡፡ ምክንያቱም የአካባቢው ማህበረሰብ በግልጽ የሚታይ የዛፍ ተከላ እና መልሶ ማልማት ስራ የሚሰራ በመሆኑ ነው፡፡ እንዲህ ያለው ጥረቶች ላይ መዋዕለ ንዋይ ቢፈስባቸው የኢትዮጵያን ‹‹ሰማያዊ ወርቅ›› ተጠርጎ ከመሔድ ለመጠበቅ ይቻላል፡፡
ምንም እንኳ በጃማ ወንዝ ዙሪያ አስቸጋሩ የአየር ንብረት እና ከፍተኛ የአፈር መሸርሸር ቢኖርም፤ በዚህ አካባቢ የሚያርሰው ማህበረሰብ እያከናወኑ ያለው የአካባቢ ጥበቃ እና የዛፍ ተከላ ጥረት የተሻሉ ለውጦችን እንደሚያመጡ ተስፋ ያደርጋሉ፡፡
ምንም እንኳ በጃማ ወንዝ ዙሪያ አስቸጋሩ የአየርንብረት እና ከፍተኛ የአፈር መሸርሸር ቢኖርም፤ በዚህ አካባቢ የሚያርሰው ማህበረሰብ እያከናወኑ ያለው የአካባቢ ጥበቃ እና የዛፍ ተከላ ጥረት የተሻሉ ለውጦችን እንደሚያመጡ ተስፋ ያደርጋሉ፡፡
The post በውሀ የሚወሰደው የኢትዮጵያ ‹ሰማያዊ ወርቅ› appeared first on InfoNile. InfoNile - Geodata journalism. Mapping stories on water issues in the Nile Basin.